ካሜሩን 2021| ለኒጀሩ የማጣሪያ ጨዋታ ለ24 ተጫዋቾች ጥሪ ተደረገ

ለካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ኒጀርን በደርሶ መልስ የሚገጥመው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለሀያ አራት ተጫዋቾች ጥሪ ማድረጉን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡ 

ከ24 ተጫዋቾች መካከል ሰዒድ ሀብታሙ፣ ዮናታን ፍስሀ፣ ግርማ ዲሳሳ እና ሚኪያስ መኮንን በዋናው ቡድን ደረጃ የመጀመርያ ጥሪ ሲደርሳቸው ይድነቃቸው ኪዳኔ እና ታደለ መንገሻ ከረጅም ጊዜ በኋላ ተጠርተዋል። አምበሉ ሽመልስ በቀለ ደግሞ ብቸኛው ከውጪ ሀገር ክለቦች የተመረጠ ተጫዋች ነው።

የተመረጡ ተጫዋቾች ዝርዝር

ግብ ጠባቂዎች (3)

ሰይድ ሀብታሙ (ጅማ አባጅፋር)
ተክለማርያም ሻንቆ (ኢትዮጵያ ቡና)
ይድነቃቸው ኪዳኔ (ወልቂጤ ከተማ)

ተከላካዮች (7)

ፈቱዲን ጀሚል (ኢትዮጵያ ቡና)
አህመድ ረሺድ (ኢትዮጵያ ቡና)
አስቻለው ታመነ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ደስታ ደሙ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
አንተነህ ተስፋዬ (ሰበታ ከተማ)
ረመዳን የሱፍ (ስሑል ሽረ)
ዮናታን ፍሰሀ (ሲዳማ ቡና)

አማካዮች (8)

ታፈሰ ሰለሞን ( ኢትዮጵያ ቡና)
ሀይደር ሸረፋ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ታደለ መንገሻ (ሰበታ ከተማ)
ግርማ ዲሳሳ (ባህርዳር ከተማ)
ይሁን እንዳሻው (ሀድያ ሆሳዕና)
ከነአን ማርክነህ (አዳማ ከተማ)
ሱራፌል ዳኛቸው ( ፋሲል ከነማ)
ሽመልስ በቀለ (ምስር አልመቃሳ /ግብፅ)

አጥቂዎች (6)

አማኑኤል ገብረሚካኤል (መቐለ70 እንደርታ )
መስፍን ታፈሰ (ሀዋሳ ከተማ)
አዲስ ግደይ (ሲዳማ ቡና)
አቤል ያለው (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ሚኪያስ መኮንን (ኢትዮጵያ ቡና)
አቡበከር ናስር (ኢትዮጵያ ቡና)

ጥሪ የደረሳቸው ተጫዋቾች የፊታችን ቅዳሜ በፌዴሬሽኑ በመገኘት ሪፖርት የሚያደርጉ ሲሆን ለዝግጅት ወደ ባህር ዳር እንደሚያመሩ ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡
© ሶከር ኢትዮጵያ