ሰበር፡ አዲስ አበባ የሚስተናገደው የፊፋ ኮንግረስ ተራዘመ

ዓለምአቀፉ የእግርኳስ አስተዳዳሪ አካል ፊፋ በመጪው ግንቦት በአዲስ አበባ ሊያካሂደው የነበረውን ስብሰባ ማራዘሙን አስታወቀ።

የዓለማችን የወቅቱ ስጋት የሆነው የኮርና ቫይረስ (COVID-19) ስርጭት እየተስፋፋ መምጣት እግርኳሱ ላይም በተለያየ መንገድ ተፅዕኖ እየፈጠረ የሚገኝ ሲሆን የተለያዩ የሊግ ውድድሮች እና የብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች እየተቋረጡ ይገኛሉ። በዚህ ቫይረስ ስርጭት ስጋት የባው ፊፋም በአዲስ አበባ ግንቦት 28 ቀን 2012 ሊያካሂደው የነበረውን ስብሰባ ወደ መስከረም 8 ቀን 2013 መራዘሙን ይፋ አድርጓል።

ፊፋ ጨምሮም የዛሬ ሳምንት ሊያካሂደው የነበረውን መደበኛ ስብሰባም ወደ ሌላ ጊዜ ማዛወሩን አስታውቋል።

© ሶከር ኢትዮጵያ