ፋሲል ከነማም እስካሁን ወደ ጎንደር አልተመለሰም

የፋሲል ከነማ የእግርኳስ ክለብ አባላት በተፈጠረው የአየር ችግር ምክንያት እስካሁን ወደ ጎንደር መመለስ አልቻሉም

ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ያለ ግብ አቻ የተለያየው ቡድኑ በ18ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በሜዳው ጎንደር ላይ ከወልቂጤ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ ጎንደር ገብተው ልምምድ መጀመር የነበረባቸው ቢሆንም ከጎረቤት ሀገራት የተነሳውና በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ላለፉት ቀናት በተከሰተው ንፋስ ምክንያት በረራዎች ለማድረግ አስቸጋሪ በመሆኑ ወደ ጎንደር መመለስ አልቻሉም።

ዐፄዎቹ የአየር ሁኔታው የማይሻሻል ከሆነ ነገ በየብስ ትራንስፖርት በመጠቀም በአውቶብስ ወደ ጎንደር ይጓዛሉ ተብሎ ይጠበቃል ።

© ሶከር ኢትዮጵያ