የወልቂጤ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የቦርድ ዋና ፀሀፊ ወደ ኃላፊነታቸው ተመልሰዋል

የወልቂጤ ከተማ የበላይ አመራሮች፣ የዞኑ አስተዳደር፣ የክለቡ ስራ አስኪያጅ እና የቡድኑ የልብ ደጋፊዎች በቅርቡ ራሳቸውን ከኃላፊነት አንስተው ከነበሩት አቶ አበባው ሰለሞን እና ረ/ፕ ጌቱ ደጉ ጋር ውይይት ካደረጉ በኋላ ወደ ሥራቸው በድጋሚ ተመልሰዋል።

በ14ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ወልቂጤ ከተማ በሜዳው ሲዳማ ቡናን አስተናግዶ 1-0 በተሸነፈበት ጨዋታ ላይ የተወሰኑ የወልቂጤ ደጋፊዎች በአመራሩ ላይ ጠንከር ያለ ተቃውሞ መግለፃቸውን ተከትሎ ሁለቱ አመራሮች በድርጊቱ ደስተኛ እንዳልሆኑ እና ራሳቸውን ከክለቡ እንዳገለሉ መዘጋባችን የሚታወስ ነው።

ይህን ተከትቶ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ መሐመድ ጀማል እና የከተማው ከንቲባ ግሩም ወልደሰንበትን ጨምሮ የክለቡ አመራሮች እና የክለቡ ደጋፊዎች ተወካዮች ከሁለቱ አመራሮች ጋር በመነጋገር የነበረውን ችግር መፍታት መቻላቸው የተገለፀ ሲሆን ራሳቸውን ባገለሉበት ደብዳቤ መሟላት አለባቸው ያሏቸው ቅድመ ሁኔታዎች እንዲሟሉ በመተማመን አቶ አበባው ሰለሞን እና ረ/ፕሮፌሰር ጌቱ ደጉ ወደ ቀድሞ ቦታቸው በመመለስ ሥራቸውን ዛሬ ጀምረዋል።

© ሶከር ኢትዮጵያ