ወልዋሎ የዲሲፕሊን ቅጣት ተላልፎበታል

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 16ኛው ሳምንት ወልዋሎ ከሰበታ ከተማ ጋር በሜዳው 2-2 አቻ በተለያየበት ጨዋታ በተፈፀመ የስፖርታዊ ጨዋነት ጥሰት ቅጣት ተላልፎበታል፡፡

የዲሲፕሊን ኮሚቴው በጨዋታው የወልዋሎ ደጋፊዎች የተጋጣሚ ቡድን ተጫዋች የሆነው ፍፁም ገብረማርያምን ስም እየጠሩ ፀያፍ ስድብ የተሳደቡ መሆናቸው እንዲሁም ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ የራሳቸውን ክለብ በመቃወም ወደ ሜዳ ድንጋይ መወርወራቸው በጨዋታ አመራሮች ሪፖርት በመደረጉ ወልዋሎን ጥፋተኛ በማለት አንድ የሜዳውን ጨዋታ አወዳዳሪው አካል በሚወስነው ገለልተኛ ሜዳ እንዲጫወት እንዲሁም 35 ሺህ የገንዘብ ቅጣት ወስኖበታል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ