ዘሪሁን ሸንገታ በቅዱስ ጊዮርጊስ ወጣት እና ታዳጊ ቡድኖች አሰልጣኝነት ተመድበዋል

ባለፈው ሳምንት የዋናው ቡድን አሰልጣኞችን ከቦታቸው ያነሳው ቅዱስ ጊዮርጊስ ምክትል አሰልጣኝነት ሲሰሩ የቆዩት ዘሪሁን ሸንገታን ከ20 ዓመት እና 17 ዓመት በታች ቡድኑ አሰልጣኝ አድርጎ መመደቡን አስታውቋል።

አሰልጣኝ ዘሪሁን የሁለቱንም የዕድሜ እርከን ቡድኖች እንደሚያሰለጥኑ የተገለፀ ሲሆን ባሳለፍነው እሁድ በአአ ከ17 ዓመት በታች ውድድር ላይ ቡድኑን ሲመሩ የታዩት አሳምነው ገብረወልድ በረዳትነት መመደባቸውንም ክለቡ ጨምሮ ገልጿል።

የ20 ዓመት በታች ቡድን አሰልጣኝ የነበሩት ደረጄ ተስፋዬ የዋናው ቡድኑን በጊዜያዊነት እያሰለጠኑ እንደሚገኙ የሚታወቅ ሲሆን በረዳት አሰልጣኝነት መመደባቸውን ክለቡ አስታውቋል። አዲስ አሰልጣኝ ክለቡን ሲቀላቀልም በረዳትነታቸው እንደሚቀጥሉ ይጠበቃል።

ከክለቡ ጋር በተያያዘ ዜና የቀድሞ የፈረሰኞቹ አንበል ሳምሶን ሙሉጌታ ከ17 ዓመት ቡድኑን እንዲመራ መወሰኑን መዘገባችን ይታወቃል። ሆኖም ሳምሶን የአሰልጣኝነት ፈቃድ የሌለው በመሆኑ ፍቃድ እስኪጨርስ ድረስ በአሰልጣኝ ቡድን ውስጥ አባል ሆኖ እንደሚሰራ ሰምተናል።

© ሶከር ኢትዮጵያ