ሀዋሳ ከተማ አዲስ ረዳት አሰልጣኝ ሾሟል

ሀዋሳ ከተማ በአምጣቸው ኃይሌ ምትክ ጊዜያዊ አሰልጣኝ የነበረው ብርሀኑ ወርቁን የሙሉጌታ ምህረት ረዳት አድርጎ ሾሟል።

ከዚህ ቀደም በተጫዋችነት ከዋና አሰልጣኙ ሙሉጌታ ምህረት ጋር በሀዋሳ የተጫወተው ብርሀኑ ወርቁ ከሴቶች ቡድን ረዳት አሰልጣኝነት ጀምሮ ከ17 እና ከ20 ዓመት ቡድኖችን ይዞ ሲያሰለጥን የነበረ ሲሆን ከአሰልጣኝ አዲሴ ካሳ ስንብት በኃየኋላ በጊዜያዊ አሰልጣኝነት ሁለት ጨዋታዎችን የመራ ሲሆን አሁን ደግሞ ረዳት አሰልጣኝ በመሆን ተሹሟል፡፡

ለረጅም ዓመታት ከታዳጊ ቡድን ጀምሮ በመስራት ረጅም ቆይታ ያደረገው እና ባለፉት ዓራት አመታት ደግሞ በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ስር የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ በአሰልጣኝ አዲሴ ካሳ ስር ደግሞ ረዳት አሰልጣኝ የነበረው አምጣቸው ኃይሌን ማሰናበቱን ስራ አስኪያጁ አቶ ጠሀ አህመድ በተለይ ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ