ኤፍሬም አሻሞ ለጎዳና ተዳዳሪዎች ድጋፍ አድርጓል

የመቐለ 70 እንደርታው የመስመር አጥቂ ኤፍሬም አሻሞ በመቐለ ከተማ ለሚገኙ የጎዳና ተዳዳሪዎች ድጋፍ አድርጓል፡፡

በአለማችንም ሆነ በሀገራችን አስከፊነቱ እያየለ የመጣውን የኮሮና ቫይረስን ለመግታት በርካታ የቅድመ መከላከል ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን በሀገራችንም ይህ በጎ ተግባር እየተተገበረ ይገኛል፡፡ በስፖርቱ ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶች ተቋማት ክለቦች፣ የክለብ ተጫዋቾች እና አሰልጣኞች በተለያየ መልኩ ድጋፍ እያደረጉ ሲሆን የመቐለ 70 እንደርታው የመስመር አጥቂ ኤፍሬም አሻሞም በመቐለ ከተማ ለሚገኙና ልዩ ማቆያ ተሰርቶላቸው ላሉ የጎዳና ተዳዳሪዎች የንፅህና መጠበቂያ፣ አልባሳት፣ ምግብ ነክ እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ዛሬ አመሻሽ ከባለቤቱ ጋር በመሆን አበርክቷል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ