ሀዲያ ሆሳዕና የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል

ሀዲያ ሆሳዕና እግር ኳስ ክለብ ለኮሮና መከላከል የሚውል የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡

ክለቡ በሀድያ ዞን አካባቢ ስርጭቱን ለመከላከል ለሚደረጉ ተግባራት ለተቋቋመው ግብረ ሀይል ከተጫዋቾች፣ ከአሰልጣኝ እና የስፖርቱ ፅህፈት ቤት ሰራተኞች ጨምሮ ከደመወዛቸው 50% በድምሩ 445,366 (አራት መቶ አርባ አምስት ሺህ ሶስት መቶ ሰላሳ ስድስት ብር) የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡ የቡድኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ለሶከር ኢትዮጵያ እርዳታው ቀጣይነት እንዲሚኖረው አያይዞ የገለፁ ሲሆን የስፖርት ቤተሰቡ በቤት በመሆን ይህን ክፉ ጊዜ እንዲሳልፈውም አያይዘው ገልፀዋል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ