ሀዋሳ ከተማ አዲስ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሾመ

ሀዋሳ ከተማ አቶ ሁቴሳ ኡጋሞን ዋና ሥራ አስኪያጅ በማድረግ ሾሟል፡፡

በቅርቡ ለረጅም ዓመታት በዋና ሥራ አስኪያጅነት ሲመሩ የነበሩት አቶ ጠሀ አህመድን ከሀላፊነት ያሰናበተው ሀዋሳ ከተማ በምትኩም አዲስ ዋና ስራ አስኪያጅ በቦታው ሾሟል። አቶ ኡቴሳ ኡጋሞ በተሰናባቹ ቦታ የተተኩ አዲሱ ስራ አስኪያጅም ሆነዋል፡፡ ከዚህ ቀደም የሀዋሳ ከተማን በፕሪምየር ሊጉ በቡድን መሪነት ያገለገሉት አቶ ኡቴሳ ከዋናው ቡድን በተጨማሪን የታዳጊ ቡድኖችም ሲሆን ያለፉትን ሁለት ዓመታት ደግሞ የክለቡን የቅርጫት ኳስ ክለብ በተመሳሳይ በሀላፊነት ሲመሩ ከቆዩ በኃላ አሁን ደግሞ ክለቡን በዋና ስራ አስኪያጅነት እንዲያገለግሉ ተሹመዋል፡፡

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ