ፌዴሬሽኑ ለመንግስት ደብዳቤ አስገብቷል

በኮሮናና ቫይረስ ምክንያት ሁሉም ውድድሮች መቋረጣቸውን ተከትሎ ፌዴሬሽኑ ለመንግስት አካለት ምላሽ ያስፈልጋል ባለው ጉዳይ ዙርያ ደብዳቤ አስገብቷል።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በመቋረጡ ምክንያት ለወትሮም ደካማ የፋይናንስ መሰረት ላይ የቆሙት ክለቦች ከፍተኛ የሆነ የፋይናስ ቀውስ ያጋጠማቸው ሲሆን ለተጫዋቾች የወራት ደሞዝ ለመክፈልም ሆነ እንደ ክለብ የመቀጠል አደጋ ውስጥ ይገኛሉ። ይህን የተረዳው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በስሩ ለሚገኙት ለፕሪምየር ሊግ ሴት እና ወንዶች፣ ከፍተኛ ሊግ ፣ ለአንደኛ ሊግ ክለቦች መንግስት ካጋጠማቸው የፋይናስ ዕጥረት እንዲያገግሙ የገንዘብ ድጎማ ሊያደርግላቸው ይገባል በማለት ለኢፊዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ደብዳቤ አስገብቷል። ከመንግስት በጎ ምላሽ እንደሚገኝበት ተስፋ የተጣለበት ይህ ደብዳቤ በቅርቡ ከሚመለከተው አካል ምላሽ እንደሚሰጠው ሰምተናል።

በሌላ ዜና በቅርቡ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከእግርኳሱ የበላይ አካል ፊፋ የገንዘብ ድጎማ እንደተደረገለት ተሰምቷል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ