ለአንድ ወር የሚቆየው የምገባ መርሐ ግብር በይፋ ተጀምሯል

(መረጃው የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት ነው።)

የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ፣ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና የቢጂ አይ ኢትዮጵያ በጋራ በመሆን በቀን አንዴ ጊዜ 300 ለሚሆኑ በአዲስ አበባ ስታዲየም ዙርያ ለሚገኙ የጎዳና ተዳዳሪዎች የተዘጋጀው የምገባ ፕሮግራም ዛሬ ተጀምሯል።

ለአንድ ወር የሚቆየውን የጎዳና ተዳዳሪዎች እና አቅመ ደካሞችን በጋራ መመገብ ፕሮግራሙን ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም ሲጀመር የኢፌዴሪ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤልያስ ሽኩር ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ስፖርት ኮሚሽነርኮ ዮናስ አረጋይ ፣ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ፣ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ፣ የቢጂአይ ኢትዮጵያ ተወካይና ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በመክፈቻው ተገኝተዋል።

ይህ ድጋፍ በቀጣይ በተቋቋሙ ኮሚቴዎች እየተገመገመ ቢያንስ በቀን ሁለቴ እንዲመገቡ እንደሚሰራ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ኤልያስ ሽኩር ተናግረዋል። በሽታውን ለመቆጣጣር የሚደረገውን ሁሉ እናድርግ ያሉት ኮሚሽነሩ ለተደረገው ድጋፍ እና በዚህ በጎ ተግባር ላይ ለተሰማሩ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ