የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዕጣ ፈንታን ለመወሰን ምክክር ሊደረግ ነው

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቀጣይ እጣ ፈንታ ዙርያ በሚቀጥለው ሳምንት መጀመሪያ ላይ የሊግ ኮሚቴው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ምክክር እንደሚያደርግ ታውቋል።

የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) አባል ሀገራት የውስጥ ሊጎቻቸውን ቀጣይ እጣፈንታን እስከ ሜይ 5 (ሚያዚያ 27) እንዲያሳውቁ በላከው ደብዳቤ መሰረት ከወዲሁ አንዳንድ ሀገራት ውሳኔዎቻቸውን ያሳወቁ ሲሆን በቀጣይ ቀናት የተጨማሪ ሀገራት ቁርጥ ያለ ውሳኔ ይጠበቃል። ይህን ተከትሎ የሊግ ኮሚቴው በቀነ ገደቡ ዋዜማ ውይይት ለማድረግ አስቧል። 17ኛው ሳምንት ላይ የተቋረጠው ውድድር ከውይይቱ በኋላ ውሳኔ ላይ ተደርሶ ለካፍ እንደሚያሳውቅ ይጠበቃል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ