ኢትዮጵያን ፉትቦለርስ አሶሴሽን ለእግር ኳስ ፌደሬሽኑ ደብዳቤ ልኳል

ከተመሰረተ 9 ወራት ያስቆጠረው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾች ማህበር ዛሬ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ደብዳቤ አስገብቷል።

አሶሴሽኑ በደብዳቤው እንደገለፀው አባላቶቹ (ተጨዋቾች) ከክለቦቻቸው ተለይተው በየቤታቸው እንደሚገኙ አስታውሶ ነገር ግን ክለቦቻቸው ተገቢውን ደሞዝ እየከፈሏቸው እንዳልሆነ አመላክቷል። በተለይ አንዳንድ ተጨዋቾች በዚህ ምክንያት ለችግር እየተዳረጉ እንደሆነ ገልጿል። ከዚህም መነሻነት የእግር ኳስ ፌደሬሽኑ ጉዳዩን ተመልክቶ በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት ብይኖችን እንዲሰጥ ጠይቀዋል። አሶሴሽኑ ለእግር ኳስ ፌደሬሽኑ ደብዳቤውን ከመላኩ በተጨማሪ ለኢፌዴሪ ስፓርት ኮሚሽን፣ ለስፖርት ሚኒስቴር እና ለማህበራዊ ጉዳይ ኮሚቴ ግልባጭ አስቀምጧል።

ሙሉ ደብዳቤ

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ