ደቡብ ፖሊስ ድጋፍ አደረገ

የከፍተኛ ሊጉ ክለብ ደቡብ ፖሊስ ለሁለተኛ ጊዜ የቁሳቁስ ድጋፍ እንዲሁም የደም ልገሳን አከናውኗዋል፡፡

ከወራት በፊት የቁሳቁስ ድጋፍን ከሀዋሳ ከተማ ክለብ ጋር በአንድ በተዘጋጀ ፕሮግራም ላይ ለግሶ የነበረው የከፍተኛ ሊግ ተወዳዳሪው ደቡብ ፖሊስ አሁን ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ የክለቡ ተጫዋቾች፣ አሰልጣኞች፣ የክለቡ ሰራተኞች በጠቅላላው ከደመወዛቸው ላይ 10% በመቁረጥ የተለያዩ የእህል ምግቦችን እና ቁሳቁሶችን በመግዛት ለአቅመ ደካሞች እንዲውል አበርክተዋል፡፡ የቡድኑ አጠቃላይ አባላትም በክለቡ ስም ብሔራዊ የደም ባንክ ያቀረበውን የደም ዕጥረት ጥያቄ መነሻ በማድረግ የመለገስ ተግባርንም ፈፅመዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የክለቡ ተጫዋቾች እና አሰልጣኞች ይሄ አስከፊ ወቅት እስኪያልፍ ድረስ ከደመወዛቸው ላይ 10% ቅናሽ በማድረግ ለክለቡ ገቢ እንዲሆን አድርገዋል፡፡

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ