አዲስ አበባ ሊካሄድ የነበረው የፊፋ ኮንግረስ በቪድዮ ኮንፈረንስ ይከናወናል

ወደ መስከረም ወር የተሸጋገረው የፊፋ ኮንግረስ በኦንላይን የመገናኛ ዘዴ እንደሚከናወን አስታውቋል።

በዚህ ወር አዲስ አበባ አስተናጋጅነት ሊከናወን የነበረው ይህ ኮንግረስ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ወደ መስከረም 28 ቀን 2013 ተሸጋግሮ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ በቪድዮ ኮንፈረንስ አማካኝነት እንደሚከናከን ፊፋ አስታውቋል። ፊፋ ይህን ከማለቱ በቀር ግን የሰጠው ተጨማሪ መረጃ የለም።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ