የአዳማ ከተማ ደሞዝ አከፋፈል ቅሬታ አስነስቷል

ለወራት ደሞዝ መክፈል የተቸገረው አዳማ ከተማ የተወሰነ ወራት ደሞዝ ቢከፍልም አሁንም በተጫዋቾች ዘንድ ቅሬታ እየፈጠረ ይገኛል።

በሁለቱ ሁለቱ ፆታ ደሞዝ ለመክፈል የተቸገረው አዳማ ከተማ ዛሬ ዕለት የሁለት ወር ደሞዝ ክፍያ መፈፀሙን ለማወቅ ችለናል። የሴቶቹ የአምና የሁለት ወር ዘንድሮ የሦስት ወር በድምሩ የአምስት ወር ቀሪ ደሞዝ ቢኖርም በዛሬው ዕለት የሁለት ወር ደሞዛቸውን መከፈሉን ለማወቅ ችለናል።

በወንዶቹ በኩል ያልተከፈለ ቀሪ የአራት ወር ደሞዝ ቢኖርም በተመሳሳይ እንደ ሴቶቹ የሁለት ወር ደሞዝ ሊከፍላቸው ችሏል። ሆኖም ከቡድኑ አባላት መካከል ስምንት ተጫዋቾች ብቻ ተለይተው ያለፍቃዳቸው እና ያለምንም ስምምነት ከደሞዛችን 80% በመቀነስ 20% ብቻ ገቢ ማድረጉ በተጫዋቾቹ በኩል ቅሬታ አስነስቷል።

ይህ ተገቢ አይደለም የሚሉት ስምንቱ ተጫዋቾች “ከእኛ ፍቃድ ውጭ 80% መቀነሱ አግባብ አይደለም በማለት ለክለቡ አመራሮች ለመግለፅ ብናመራም የሚያናግረን አካል አጥተናል።” በማለት ቅሬታቸውን ወደ ፌዴሬሽኑ የክስ ደብዳቤ በመያዝ ሰኞ እንደሚቀርቡ ሰምተናል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ