ፕሪምየር ሊጉ እና ፌዴሬሽኑ በፎርማት ለውጥ ዙርያ መከሩ

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እና የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኩባንያ ሰሞኑን ስብሰባ ማድረጋቸው ታውቋል።

የስብሰባው ዋና አላማ በቀጣይ የኢትዮጵያ ሊጎች የሚጓዙበት መንገድ ላይ መምከር ሲሆን ከኮቪድ-19 ስርጭት መቆጣጠር ከተቻለ በኋላ በምን አይነት አካሄድ ውድድሮች መከናወን ይኖርባቸዋል የሚል ውይይት መደረጉን ሰምተናል። ምናልባትም አሁን እየተከናወነበት የሚገኘው ፎርማት ሊለወጥ እንደሚችልም ተገምቷል።

የውይይቱ ዝርዝር ሀሳብ እና ውሳኔዎች በቀጣይ እንደሚገለፁ የሚጠበቅ ሲሆን አንዳንድ ክለቦች እያደረጉት ከሚገኙት የዝውውር እንቅስቃሴ በተቃራኒ አመዛኞቹ ክለቦች የፎርማቱ ሁኔታ ከለየለት በኋላ ወደ ዝውውር ለመግባት እንዳሰቡ ተሰምቷል።

በ1936 የተጀመረውና ከአፍሪካ ቀደምት ሊጎች አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ የሊግ ውድድር በምስረታው ዓመታት በአዲስ አበባ ክለቦች ብቻ ሲደረግ ቆይቶ በ1940ዎቹ አጋማሽ በሦስት ከተሞች ደርሶ መልስ የተካሄደ ሲሆን ከስልሳዎቹ እስከ 1989 ድረስ የየክፍለ ሀገራት ሻምፒዮና ተደርጎ በማጠቃለያ ውድድር አሸናፊው እንዲለይ ተደርጓል። ከ1990 ጀምሮ ደግሞ ላለፉት 22 ዓመታት ደግሞ በወጥነት በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ክለቦች በደርሶ መልስ ውድድራቸውን እያከናወኑ ይገኛሉ።

ሶከር ኢትዮጵያ ጉዳዩን እየተከታተለች የሚኖሩትን አዳዲስ መረጃዎች የምናደርሳችሁ መሆኑን እንገልፃለን።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ