አሰልጣኝ ገብረመድኅን ኃይሌ ለመቀጠል ተስማምተዋል

ላለፉት ሁለት ዓመታት ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር ቆይታ አድርገው ቡድኑ የሊጉን ዋንጫ እንዲያነሳ ያስቻሉት አሰልጣኝ ገብረመድኅን ኃይሌ ከቡድኑ ጋር ለመቀጠል ተስማምተዋል።

በ2010 ከጅማ አባጅፋር ጋር የሊጉ ዋንጫ ባነሱበት ማግስት ወደ መቐለ 70 እንደርታ በማምራት በተከታታይ የሊጉን ክብር ያሳኩት አሰልጣኙ ላለፉት ሁለት ሳምንታት በመቐለ ይቆያሉ ወይስ ወደ ሌሎች የፕሪምየር ሊግ ክለቦች ያመራሉ የሚል ጥያቄ እየተነሳ ቢቆይም በመጨረሻም ከምዓም አናብስት ጋር ለመቀጠል መስማማታቸውን ለማወቅ ችለናል።

በሰማንዎቹ መጨረሻ ከአስደናቂው የእግርኳስ ተጫዋችነት ሕይወታቸው ከተገለሉ በኋላ በመቐለ ከነማ (ምክር ቤት) አሰልጣኝነት ጀምረው በኋላ ላይ የሥም ለውጥ ባደረገው ትራንስ ኢትዮጵያ ፣ ባንኮች ፣ ኢትዮጵያ ቡና ፣ ደደቢት ፣ መከላከያ ፣ ጅማ አባቡና ፣ ጅማ አባጅፋር ፣ በየመን ክለብ እና ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ማሰልጠን የቻሉት አሰልጣኝ ገብረመድኅን ከመቐለ ጋር መቀጠላቸውን ተከትሎ ክለቡ በቀጣይ ቀናት ወደ ዝውውር ገበያው በስፋት ይቀላቀላል ተብሎ ይጠበቃል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ