ሰበታ ከተማ የወጣቱን ተከላካይ ውል አራዘመ

ሰበታ ከተማዎች የመስመር ተከላካዩ ኃ/ሚካኤል አደፍርስን ውል ለተጨማሪ ዓመት አራዝመዋል፡፡

ከሰበታ ከተማ የታዳጊ ቡድን የተገኘው ኃይለሚካኤል በ2011 ክለቡ በከፍተኛ ሊግ ተወዳዳሪ እያለ አድጎ መጫወት የጀመረ ሲሆን በተሰረዘው የዘንድሮው ፕሪምየር ሊግ መልካም ዓመትን ማሳለፍ ችሏል። ይህን ተከትሎም ውሉ ለተጨማሪ ዓመት ታድሶለታል፡፡

የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ ዓለማየሁ ምንዳ እንደገለፁልን ከነገ ጀምሮ በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ እየተመራ የነባር ተጫዋቾችን ውል ወደማራዘሙ እንደሚገባ ነግረውናል፡፡

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ