ለሀዲያ ሆሳዕና ለመፈረም ተስማምቶ የነበረው መሳይ አያኖ በሲዳማ ቡና ውሉን ዛሬ አራዘመ

ትናንትት ወደ ሆሳዕና ለማምራት ተስማምቶ የነበረው ግብ ጠባቂው መሳይ አያኖ በሲዳማ ቡና ውሉን አራዝሟል፡፡

ደቡብ ፖሊስን ከለቀቀ በኃላ ከ2010 ጀምሮ ለሲዳማ ቡና በመጫወት ላይ የሚገኘው ተጫዋቹ ዘንድሮ ውሉ በሲዳማ ቤት መጠናቀቁን ተከትሎ ለመቀጠል ስምምነት ላይ ደርሶ የነበረ ቢሆንም ከጥቅማ ጥቅሞች ጋር በተገናኘ መግባባት ሳይችል በመቅረቱ ሆሳዕና ተገኝቶ ለሀዲያ ሆሳዕና ለመጫወት የአንድ ዓመት ቅድመ ስምምነትን መፈፀሙን ትላንት መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ሆኖም ተጫዋቹ ወደ ሀዋሳ ከተመለሰ በኃላ የነበረበት ሲዳማ ቡና የበላይ አካላት ከተጫዋቾቹ ጋር ዛሬ ረፋድ ባደረጉት ንግግር ከስምምነት ላይ በመድረሳቸው ለሁለት ተጨማሪ ዓመት ለመቀጠል መስማማቱን የክለቡ አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡

የሀዲያ ሆሳዕና ስራ አስኪያጅ አቶ መላኩ ማዶሮ በበኩላቸው ተጫዋቹ ከእኛ ጋር በቀጣዩ ዓመት ለመጫወት በክለቡ የበላይ አካላት አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ እና ወኪሉ ባሉበት ፈርሟል ቢሉም ዛሬ ለቀድሞው ክለቡ ፊርማውን ለማኖር መስማማቱ አስገራሚ ሆኗል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ

error: