ፍሬዘር ካሳ ውሉን በድሬዳዋ አድሷል

ፍሬዘር ካሳ ለተጨማሪ ዓመት በድሬዳዋ ለመቆየት ተስማምቷል፡፡

ከቅዱስ ጊዮርጊስ ታዳጊ ቡድን የተገኘው እና በዋናው ቡድንም ተጫውቶ ያለፈው የመሀል እና የመስመር ተከላካዩ ፍሬዘር ካሳ በተሰረዘው የውድድር ዓመት በግሉ ድንቅ ዓመት ያሳለፈ ሲሆን ውሉ በመጠናቀቁ ከሌሎች ክለቦች ጋር ስሙ ቢያያዝም በድሬዳዋ ለተጨማሪ ዓመት መቆየቱን ሶከር ኢትዮጵያ ከክለቡ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል ፡፡

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ