ሀዋሳ ከተማ አማካዩን ለመቆየት ተስማማ

እስካሁን የዘጠኝ ነባር ተጫዋችን ውል ለማራዘም እና ሁለት አዳዲስ ተጫዋቾችን ለማስፈረም የተስማሙት ሀዋሳ ከተማዎች የአሥረኛ ተጫዋቻቸውን ውል አራዝመዋል፡፡

አማካዩ ሄኖክ ድልቢ ውሉን በክለቡ ያራዘመ ተጫዋች ነው። ከሀዋሳ ታዳጊ ቡድን ወደዋናው ካደገ በኃላ ያለፉትን አራት የውድድር ዓመታት በክለቡ ቆይታ የነበረው ይህ ተጫዋች በተለይ ዘንድሮ ሊጉ እስከተሰረዘረበት ጊዜ ድረስ ከደመቁ ተጫዋቾች መሀከል አንዱ ነበር፡፡ ውሉ በመጠናቀቁ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ስሙ ተያይዞ የነበረው አማካዩ ለሁለት ተጨማሪ ዓመት በሀዋሳ ለመቆየት ተስማምቷል፡፡

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ