ሲዳማ ቡና የሁለት ተጫዋቾችን ውል አራዘመ

ሲዳማ ቡና የአማኑኤል እንዳለን እና ክፍሌ ኪአን ውል አድሷል፡፡

ወጣቱ የመስመር ተከላካይ አማኑኤል እንዳለ ውሉን ያራዘመ አስረኛ ተጫዋች ነው፡፡ ከሲዳማ ቡና ወጣት ቡድን ከተገኘ በኃላ ያለፉትን ሦስት ዓመታት በክለቡ ቆይታ ያደረገው ተጫዋቹ በተለይ ዘንድሮ በተሻለ ለክለቡ ወሳኝነቱን ያስመሰከረ ሲሆን ከኃላ መስመር እየተነሳ ወሳኝ ግቦችን ከመረብ ሲያሳርፍ ተመልክተናል፡፡ ተጫዋቹ ገና ቀሪ የአንድ ዓመት ውል ቢቀረውም ደመወዙ ተስተካክሎለት ለተጨማሪ ሁለት ዓመት በክለቡ ለመቆየት ተስማምቷል፡፡

ሌላኛው ውሉን ያራዘመው ተጫዋች ክፍሌ ኪአ ነው፡፡ እንደ አማኑኤል ሁሉ የሲዳማ ቡና ታዳጊ ቡድን ፍሬ የሆነው ይህ የመሐል ተከላካይ ለሲዳማ ቡና በተለየ መልኩ ከዓምና ጀምሮ በተከላካይ ክፍሉ ተጠቃሽ ተጫዋች ሲሆን ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ ለተጨማሪ ዓመት ለመቆየት ከስምምነት ደርሷል፡፡

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ