አዳማ ከተማ እና ውዝፍ ዕዳው

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከነበረው ጥንካሬ በተለያዩ ከሜዳ ውጭ በሚያጋጥሙት ፈተናዎች እየተንገዳገደ የሚገኘው አዳማ ከተማ ያልተከፈለ ውዝፍ ዕዳ ተገኘበት።

አዳማ ከተማ ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ በኢትዮጵያ እግርኳስ ውስጥ ጠንካራ ቡድን በመስራት፣ ውጤታማ ቡድን በመሆን እና ተተኪ ተጫዋቾችን በየዘመኑ በማፍራት የሚታወቅ ክለብ መሆኑ ይታወቃል። ታዲያ ይህ ጠንካራ ቡድን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በፋይናስ እጥረት ምክንያት የተለያዩ ፈተናዎች እያጋጠሙት እንደሆነ አይዘነጋም። አዲስ አመራር እና የክለብ ፕሬዝደንት የሾመው አዳማ ከተማ በአሁን ሰዓት ለሆቴሎች፣ ለስፖርት ትጥቆች እና ለተለያዩ ወጪዎች ያልተከፈሉ አስራ ዘጠኝ ሚሊዮን ብር ውዝፍ ዕዳ እንዳለበት ሰምተናል።

በዚህ ጉዳይ ላይ ክለቡ ያልተከፈለው ውዝፍ እዳ ከምን የመነጨ ነው የሚለውን ለማጣራት የክለቡን አመራሮች ለማግኘት ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት ያልተሳካ ቢሆንም በቀጣይ በዚህ ጉዳይ ላይ የክለቡ ምላሽ ይዘን የምንመለስ ይሆናል።

የአዳማ ከተማ የእዳ መጠን በዚህ ደረጃ ይታወቅ እንጂ አብዛኛዎቹ የሀገራችን ክለቦች በተለይ በዚህ አምስት ዓመታት ውስጥ ብቻ ያልተከፈለ ከፍተኛ የሆነ ውዝፍ እዳ እንዳለባቸው ይታወቃል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!