ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ኢንስትራክተሮች እነማን ናቸው?

በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በይፋ የተመዘገቡት የሀገራችን የካፍ ኢንስትራክተሮች በዝርዝር እነማን እንደሆኑ ይፋ ሆኗል።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የካፍ የስልጠና ኮንቬንሽንን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥቷል። በመግለጫው ላይም በሀገራችን የሚገኙ የካፍ ኢንስትራክተሮች ማንነት በጋዜጠኞች ተጠይቆ የእግርኳስ ፌዴሬሽኑ የጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን ስማቸውን ይፋ አድርገዋል።

የካፍ ኤሊት ኢንስትራክተር

– አብርሃም መብራቱ

ወንድ የካፍ ኢንስትራክተሮች

– ሲራክ ሀብተማርያም (ዶ/ር)
– ሰውነት ቢሻው
– መኮንን ኩሩ
– ዳንኤል ገ/ማርያም
– አብርሃም ተክለሃይማኖት
– አንተነህ እሸቴ
– ጌታቸው አበበ (ዶ/ር)

ሴት የካፍ ኢንስትራክተሮች

– ሰላም ዘርዓይ
– ሕይወት አረፋይኔ
– በኃይሏ ዘለቀ
– መሠረት ማኒ

በተያያዘም በሀገራችን ኢንስትራክተሮች የሉም እየተባለ የሚሰነዘረው ሃሳብ ስህተት እንደሆነ በመግለፃው ተመላክቷል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!