ሀዋሳ ከተማ ለሴት ቡድኑ አዳዲስ አሰልጣኞችን ቀጥሯል

የሀዋሳ ከተማ የሴቶች እግር ኳስ ክለብ ዛሬ በይፋ አዳዲስ አሰልጣኞችን መሾሙን ክለቡ አስታውቋል፡፡ ክለቡን ከምስረታው ጀምሮ ላለፉት ስምንት አመታት ሲያሰለጥን የቆየውን አሰልጣኝ ዮሴፍ ገብረወልድ ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ ነው ክለቡ አዲስ አሰልጣኝ የሾመው፡፡

አዲሱ የሴቶች ቡድን አሰልጣኝ መልካሙ ታፈረ ሆኖ ተሹሟል፡፡ አሰልጣኙ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ወቅቶች በሁለቱም ፆታ በራሱ ፕሮጀክቶችን አቋቁሞ ማሰልጠን የቻለ ሲሆን የሀዋሳ ከ15 ዓመት በታች የታዳጊ ቡድን ለሦስት ተከታታይ ዓመታት ካሰለጠነ በኃላ ዘንድሮ ደግሞ የአሰልጣኝ ዮሴፍ ገብረወልድ ረዳት ሆኖ በማገልገል ካሳለፈ በኃላ በዛሬው ዕለት በሁለት ዓመት ኮንተራንት በዋና አሰልጣኝነት ተሹሟል፡፡

ረዳት አሰልጣኝ በመሆን የተሾመው በልጉዳ ዲላ ነው፡፡ በተጫዋችነት በሲዳማ ቡና በብሔራዊ ሊግ እና በፕሪምየር ሊግ ደረጃ ተጫውቶ ወደ አሰልጣኝነቱ ከገባ በኃላ በተለያዩ የከተማው አካባቢዎች የፕሮጀክት ቡድኖች ከማሰልጠኑ ባለፈ የሲዳማ ቡና የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ረዳትም ሆኖ ከዚህ ቀደም አገልግሏል፡፡ ያለፉትን ሦስት ዓመታት የሀዋሳ የሴቶች የቢ ቡድንን ሲያሰለጥን ቆይቶ በዛሬው ዕለት የዋናው ቡድን ረዳት በመሆን ተሹሟል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!