ሙጂብ ቃሲም በዐፄዎቹ ቤት ለመቆየት ተስማምቷል

ከፋሲል ከነማ ጋር እንደሚለያይ ገልፆ የነበረው ሙጂብ ቃሲም ከክለቡ ጋር ለመቀጠል ተስማምቷል።

በፋሲል ከነማ ጋር ጥሩ ጊዜ እያሳለፈ የሚገኘው ሙጅብ ቃሲም የሁለት ዓመት ውሉን ከጨረሰ በኋላ በፋሲል ቤት ይቀጥላል አይቀጥልም የሚለው ጉዳይ ሲያወዛግብ የቆየ ሲሆን ባለፈው ሳምንት ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ባደረገው ቆይታ ከክለቡ ጋር በውል ማራዘም ጉዳይ ከስምምነት ባለመድረሳቸው ለመለያየት እንደተገደደ መግለፁ ይታወሳል። ሆኖም ከዛ ወዲህ ከክለቡ ጋር ባደረጉት ድርድር በመጨረሻም ለተጨማሪ ሁለት ዓመት በፋሲል ቤት ለመቆየት ተስማምቷል።

በተከታታይ ሁለት ዓመታት በዐፄዎቹ ቤት የክለቡ ከፍተኛ ግብ አግቢ የነበረው ሙጅብ ቃሲም በዘንድሮው የውድድር ዘመን የሊጉን ከፍተኛ ግብ አግቢነት በ14 ግቦች እየመራ ነበር የተቋረጠው።

ሙጂብ ቃሲም ከዚህ ቀደም በሲዳማ ቡና፣አዳማ ከነማ እና ሀዋሳ ከተማ እንዲሁም ያለፉትን ሁለት ዓመታት በፋሲል ከነማ መጫወቱ ይታወቃል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!