ለቀድሞ አንጋፋ ኢንተርናሽናል ዳኛ ድጋፍ ተደረገላቸው

በኢትዮጵያ ዳኞች ታሪክ ስማቸው ቀድሞ ከሚነሱ ዳኞች መካከል አንዱ የሆኑት የቀድሞ አንጋፋ ኢንተርናሽናል ዳኛ ዓለም ንፀበ ኢንጅነር ኃይለየሱስ ፍስሐ ድጋፍ አድርገውላቸዋል።

ከሰባዎቹ መጀመርያ አንስቶ በዳኝነት ዘመናቸው ትልቅ ስም የነበራቸው የቀድሞ ኢንተርናሽናል ዳኛ በዕድሜ መግፋት እና በጤና እክል ምክንያት ሁለት እግራቸው ተቆርጦ የአልጋ ቁራኛ ከሆኑ ሁለት ዓመታት ሆኗቸዋል። እኚህ አስታወሽ ያጡ አንጋፋ ዳኛን ያሉበትን ሁኔታ በመረዳት በመኖርያ ቤታቸው በመሄድ የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት ኢንጅነር ኃይለየሱስ ፍስሀ የምግብ ዘይት እና የእህል ድጋፍ ከማድረጋቸው በተጨማሪ ለበዓል ማሳለፊያ እንዲረዳቸው የአምስት ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርገውላቸዋል ።

እኝህ አንጋፋ ስመጥር ዳኛ ዓለም ንፀበ በቀጣይ ሶከር ኢትዮጵያ በዳኞች ገፅ አምዳችን ታሪካቸውን ይዘን እንደምንቀርብ ከወዲሁ ለመጠቆም እንወዳለን።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!