ከፍተኛ ሊግ ምድብ 2 ፡ አአ ከተማ እና ጅማ አባቡና መብረራቸውን ሲቀጥሉ ደቡብ ፖሊስ የመጀመርያ ድሉን አስመዝግቧል

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ 7ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ትላንት እና ዛሬ ተካሂደዋል፡፡ አአ ከተማ ከነገሌ የ3-1 ውጤት ይዞ ሲመለስ ጅማ አባ ቡና በአስገራሚ ሁኔታ ከመመራት ተነስቶ አሸንፏል፡፡ ደቡብ ፖሊስም የውድድር ዘመኑን የመጀመርያ ድል አስመዝግቧል፡፡

ወደ ነገሌ የተጓዘው አዲስ አበባ ከተማ ነገሌ ቦረናን 3-1 በመርታት መሪነቱን አስጠብቋል፡፡ የመዲናዋን ክለብ የድል ግቦች ፍጹም ካርታ ሁለት ፣ ዳንኤል አባተ አንድ ሲያስቆጥሩ የነገሌ ቦረናን ብቸኛ ግብ ያስቆጠረው ዳግም በቀለ ነው፡፡ ፍጹም ዛሬ ሁለት ግብ ማስቆጠሩን ተከትሎ የግብ መጠኑን 5 ሲያሰደርስ ዳግም በቀለ 6ኛ ግቡን አስቆጥሯል፡፡ አዲስ አበባ ከተማ ነጥቡን 18 አድርሶ የሊጉን መሪነት ከጅማ አባ ቡና በ1 ነጥብ በመብለጥ ምድቡን መምራቱን ቀጥሏል፡፡

ጅማ ስታድየም ላይ ጅንካን ያስተናደው ጅማ አባ ቡና 3-2 አሸንፎ አዲስ አበባ ከተማን እግር በእግር መከተሉን ቀጥሏል፡፡ ጅንካዎች በሃቁምንይሁን ገዛኸኝ እና ሚልዮን መንገሻ ግቦች ባለሜዳው አባቡናን 2-0 ለመምራት ፈጀባቸው ከ15 ያነሰ ደቂቃ ብቻ ነበር፡፡ ጅማ አባ ቡናዎች በሁለተኛው አጋማሽ ኪዳኔ አሰፋ ፣ በቢንያም ኃይሌ እና ሳምሶን ተረፈ ግቦች የጅንካን 2-0 መሪነት በመቀልበስ 3-2 ማሸነፍ ችለዋል፡፡ ነጥባቸውን 17 በማድረስም 2ና ደረጃቸውን አስጠብቀዋል፡፡

ሻሸመኔ በተከታታይ ጨዋታዎች ነጥብ መጣሉን ቀትሎበታል፡፡ ድሬዳዋ ላይ ናሽናል ሴሚንትን የገጠመው ሻሸመኔ 2-0 ተሸንፏል፡፡ የናሽናል ሴሚንትን ድል ግቦች ከመረብ ያሳረፈው አብነት መንግስቱ ነው፡፡

ወራቤ ላይ ድሬዳዋ ፖሊስን ያስተናገደው ወራቤ ከተማ ካለግብ አቻ ተለያይቷል፡፡

ባለፈው ሳምንት ከባድ ሽንፈት ያስተናገደው ሀላባ ከተማ ነቀምት ከተማን 2-1 በማሸነፍ ደረጃውን አሻሽሏል፡፡ ለሀላባ አበበ ታደሰ እና እዮብ በቀታ ሲያስቆጥሩ የነቀምትን ግብ ማንያዘዋል ጉዳዩ ከመረብ አሳርፏል፡፡

ባለፈው ሳምንት ወደ አሸናፊነት ተመልሶ የነበረው ጅማ ከተማ ወጥ አቋም ማሳየት አልቻለም፡፡ ወደ አርሲ ነገሌ ተጉዞም የ2-1 ሽንፈት ደርሶበታል፡፡ የአርሲ ነገሌን ድል ግቦች በተሰለፈባቸው ጨዋታዎች ግብ አስቆጥሮ መውጣት ልማድ ያደረገው አገኘሁ ልኬሳ እና ሚልዮን አስማኤል ሲያስቆጥሩ አላዛር ዘውዴ የጅማን ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡ አገኘሁ ለአረሲ ካደረጋቸው 6 ጨዋታዎች በ5ቱ ግብ በማስቆጠር ለአርሲ ወሳኝ ተጫዋችነቱን አስመስክሯል፡፡

የዚህ ምድብ ሁለት ጨዋታዎች ትላንት በአበበ ቢቂላ ላይ የተካሄዱ ሲሆን በ8፡00 ደቡብ ፖሊስ አአ ዩኒቨርሲቲን በማሸነፍ ከወራጅ ቀጠናው ወጥቷል፡፡ ወንድሜነህ አይናለም ሁለት ግቦች ሲያስቆጥር ምስጋና ወልደዮሃንስ አንዷን ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡ ድሉ ለደቡብ ፖሊስ በውድድር ዘመኑ የመጀመርያ ሲሆን ወንድሜነህ አይናለም ያስቆጠራቸው 6 ግቦች ከነገሌ ቦረናው ዳግም በቀለ ጋር በጋራ የዚህን ምድብ ከፍተኛ ግብ አግቢነት እንዲመራ አስችሎታል፡፡

በ10፡00 ባቱ ከተማን ያስተናገደው ፌዴራል ፖሊስ 1-1 አቻ ተለያይቷል፡፡ ባቱ ክንዴ አቢቾ ባስቆጠረው ግብ እስከ ጨዋታው መጠናቀቅያ ደቂዎች ድረስ መምራት ቢችልም ቻላቸው ቤዛ በ87ኛው ደቂቃ ፌዴራል ፖሊስ አቻ አድርጓል፡፡

የምድብ ለ የደረጃ ሰንጠረዥ ይህንን ይመስላል፡-

HL B

ፎቶ – የውድድር ዘመኑን የመጀመርያ ድል ያስመዘገበው ደቡብ ፖሊስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *