የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ስብስብ ወደ 25 ተጫዋቾች ተቀንሷል

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ለ2016 የካሜሩን የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ማጣርያ የሚያደርገውን ዝግጅት ቀጥሏል፡፡ አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው ከ2 ሳምንት በፊት ከመረጧቸው 30 ተጫዋቾች መካከል 5 ተጫዋቾችን በመቀነስ 25 ተጫዋቾችን የያዙ ሲሆን የኤሌክትሪኳ ፅዮን ፈየራ ፣ የዳሽን ቢራዋ ሰርካዲስ ጉታ ፣ የደደቢቷ ፍሬወይኒ ገብረመስቀል እና የአዳማ ከተማዋ ገነት ፍርዴ ተቀንሰዋል፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊሷ ትዕግስት ዘውዴ ሪፖርት ማድረግ በነበረባት የጊዜ ገደብ ባለማድረጓ ቀደም ብላ መቀነሷ የሚታወስ ነው፡፡ 

ሉሲዎቹ በሱሉልታ የሚያደርጉት ዝግጅት እስከ ረቡዕ ድረስ የሚቀጥል ሲሆን ከሐሙስ ጠዋት ጀምሮ የልምድ ስፍራቸውን አዲስ አበባ ስታድየም ላይ ያደርጋሉ፡፡

የሉሲዎቹ የ25 ተጫዋቾች ስብስብ ይህንን ይመስላል፡-

ግብ ጠባቂዎች

ዳግማዊት መኮንን – የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ንግስት መዓዛ – የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ታሪኳ በርገና – ድሬዳዋ ከተማ

 

ተከላካዮች

ውባለም ፀጋዬ – ደደቢት

መስከረም ኮንካ – ደደቢት

አሳቤ ሞሶ – ዳሽን ቢራ

ፋሲካ በቀለ – ዳሽን ቢራ

ፅዮን እስጢፋኖስ- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ጥሩነሽ መንገሻ – የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

እፀገነት ብዙነህ – የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ሀብታም እሸቱ – የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

 

አማካዮች

ህይወት ደንጊሶ – የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ቅድስት ቦጋለ – የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ብሩክታዊት ግርማ – የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ብርቱካን ገ/ክርስቶስ- ደደቢት

ኤደን ሽፈራው – ደደቢት

እመቤት አዲሱ – መከላከያ

አዲስ ንጉሴ – ሀዋሳ ከተማ

የካቲት መንግስቱ – ሲዳማ ቡና

 

አጥቂዎች

ሽታዬ ሲሳይ – የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ረሒማ ዘርጋ – የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ሎዛ አበራ – ደደቢት

መዲና አወል – ቅድስተ ማሪያም

ሔለን እሸቱ – ዳሽን ቢራ

ትደግ ፍስሃ – ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *