ሰበታ ከተማ ግብ ጠባቂ አስፈረመ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ምንተስኖት አሎ ሰበታ ከተማን ተቀላቀለ፡፡

አሰልጣኝ ውበቱ አባተን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሳልፈው የሰጡት ሰበታ ከተማዎች በጥቂት ቀናቶች ውስጥ አዲስ አስልጣኝ ይቀጥራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለም ክለቡ ራሱን ለማጠናከር በስራ አስኪያጁ አቶ ዓለማየሁ ምንዳ እና ሌሎች የቴክኒክ አባላት አማካኝነት በዛሬ ዕለት ግብ ጠባቂ ለሁለት አመት አስፈርሟል፡፡ ምንተስኖት አሎ አዲሱ የሰበታ ከተማ ግብ ጠባቂ ሆኗል፡፡በባህርዳር ከተማ መልካም የውድድር ዓመታትን ካሳለፈ በኃላ የተሰረዘውን የውድድር ዓመት ወደ ስሑል ሽረ በመጓዝ ቆይታን ያደረገው ተጫዋቹ በክለቡ ቆይታው ለሙከራ ወደ ቱርክ አቅንቶ መመለሱም ይታወሳል።

ከበርካታ ክለቦች ጋር ስሙ ሲያያዝ ቆይቶም ሰበታ ከተማን በይፋዊ ፊርማ ከሰዓታት በፊት ተቀላቅሏል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!