ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | አዳማ ከተማ የአሰልጣኙ እና አምስት ተጫዋቾችን ውል ለማደስ ተስማማ

የአዳማ ከተማ ሴቶች ቡድን የአሰልጣኝ ሳሙኤል አበራን ውል ለተጨማሪ ዓመት ለማራዘም ሲስማማ የአምስት ነባር ጫዋቾትንም ውል ለማደስ ከስምምነት ደርሷል።

በ2011 አዳማ ከተማን ቻምፒዮን ያደረገው አሰልጣኝ ሳሙኤል አበራ በአዳማ ከተማ ውሉን ማጠናቀቁን ተከትሎ ለአንድ ተጨማሪ የውድድር ዓመት ለማራዘም የተስማማ ሲሆን አምስት ተጫዋቾችም በክለቡ ፅሕፈት ቤት ተገኝተው የኮንትራት ማራዘምያ ቅድመ ውል መፈረማቸውን አሰልጣኙ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል።

ውል ያራዘሙት ተጫዋቾች ግብ ጠባቂዋ እምወድሽ ይርጋሸዋ፣ የቀኝ መስመር ተከላካይዋ እና አምበሏ ናርዶስ ጌትነት፣ የመሀል ተከላካዮቹ መስከረም ካንኮ እና ሀና ኃይሉ እንዲሁም አጥቂዋ ሳራ ነብሶ ናቸው፡፡

ክለቡ በቀጣዩ ቀናትም አዳዲስ እና ነባር ተጫዋቾችን እንደሚያስፈርም አሰልጣኙ ነግሮናል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!