አማካዩ ከሲዳማ ቡና ጋር ተለያይቷል

ከሲዳማ ቡና ጋር የተለያየው የአማካይ ሥፍራ ተጫዋቹ ትርታዬ ደመቀ ከሲዳማ ቡና ቀጣይ ማረፊያው በቅርቡ ይታወቃል፡፡

በአርባምንጭ ከተማ የእግር ኳስ ህይወቱን የጀመረው ይህ ተጫዋች 2009 ክለቡን ከለቀቀ በኃላ ወደ ሲዳማ ቡና አምርቶ እስከ ተሰረዘው 2012 የውድድር አመት ድረስ በክለቡ በመጫወት አሳልፏል፡፡ ትርታዬ ከሲዳማ ቡና ጋር የነበረው የውል ጊዜ በማብቃቱ የክለቡን አመራሮች እና ደጋፊዎች በማመስገን መለያየቱን ለሶከር ኢትዮጵያ በላከው መልዕክት ገልጿል፡፡

“ከሲዳማ ቡና ጋር ጥሩ ዓመታትን አሳልፊያለሁ፡፡ አሁን ግን አዲስ ባህል አዲስ የሆነ ክለብ ፈልጌ ተለያይቻለሁ። በክለቡ ለነበረኝ ጊዜ የክለቡን አመራሮች እና አሰልጣኞች እንዲሁም ውብ የሆነውን ደጋፊ ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡ የእኔም ቀጣይ ክለብ በአጭር ቀን ውስጥ አሳውቃለሁ።”

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!