ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | ኢትዮ ኤሌክትሪክ አምስት ተጫዋቾችን አስፈረመ

ኢትዮ ኤሌክትሪኮች በዛሬው ዕለት አምስት ተጫዋቾችን አስፈርመዋል፡፡

የቀድሞዋ የዳሽን ቢራ እና ባለፉት ዓመታት በመከላከያ እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የተጫወተችው ግብ ጠባቂዋ ማርታ በቀለ፣ በቅዱስ ጊዮርጊስ ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ አሳይታ ያለፈውን ዓመት ደግሞ በመከላከያ ቆይታ የነበራት ተከላካይዋ መሠሉ አበራ፣ ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር ከሰሞኑ ውል ለማራዘም ስምምነት ፈፅማ የነበረችው ሌላኛዋ ተከላካይ ሳምራዊት ኃይሉ፣ በሲዲማ ቡና፣ ዳሽን ቢራ፣ መከላከያ እና ያለፈውን ዓመት በጌዲኦ ዲላ ያሳለፈችው ከቀናት በፊትም ለመቐለ ለመጫወት ስምምነት ፈፅማ የነበረችው ፋሲካ በቀለ እንዲሁም በሀዋሳ ከተማ፣ ሲዳማ ቡና፣ ንግድ ባንክ እና መከላከያ በመጫወት የምናውቃት አማካይዋ የካቲት መንግስቱ በአንድ ዓመት ውል ለኢትዮ ኤሌክትሪክ የፈረሙ ተጫዋቾች ናቸው።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!