ከፍተኛ ሊግ | ደሴ ከተማ አዲስ አሰልጣኝ ሾመ

በዘንድሮው የውድድር ዓመት ደሴ ከተማን የሚመራው አሰልጣኝ ታውቋል።

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሀ ተወዳዳሪ የሆነው የሰሜኑ ክለብ ደሴ ከተማ በዛሬው ዕለት አሰልጣኝ ያሬድ ቶሌራን የክለቡ ዋና አሰልጣኝ በማድረግ በአንድ ዓመት ኮንትራት በይፋ ቀጥሯል፡፡

ከዚህ ቀደም በወልቂጤ ከተማ፣ ለገጣፎ ለገዳዲ እና 2011 ላይ የመድን ረዳት እንዲሁም የተሰረዘውን የውድድር ዓመት ደግሞ በዋና አሰልጣኝነት መድንን ሲያሰለጥን የቆየ ሲሆን ዘንድሮ ደግሞ ደሴ ከተማን እየመራ ዓመቱን የሚያሳልፍ ይሆናል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!