ከፍተኛ ሊግ | ኢትዮጵያ መድን አዲስ አሰልጣኝ ቀጠረ

በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ሐ ላይ የሚገኘው ኢትዮጵያ መድን አሰልጣኝ ፀጋዬ ወንድሙን በዋና አሰልጣኝነት ቀጥሯል፡፡

መድን የተሰረዘውን የውድድር ዓመት በአሰልጣኝ ያሬድ ቶሌራ እየተመራ ዓመቱን የጀመረ ሲሆን የኮቪድ 19 ከመግባቱ ቀደም ብሎ አሰልጣኙን አሰናብቶ ግርማ ታደሰን ቀጥሮ እንደነበር ይታወሳል፡፡ የቀድሞው የሀድያ ሆሳዕና አሰልጣኝ ሊጉ በኮቪድ 19 በመቋረጡ ከክለቡ ጋር በስምምነት በመለያየታቸው ለዘንድሮው የከፍተኛ ሊግ ውድድር አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር ክለቡ ከአስራ ዘጠኝ ቀናት በፊት የቅጥር ማስታወቂያን አውጥቶ ከሰላሳ በላይ አሰልጣኞችን ካወዳደረ በኃላ አሰልጣኝ ፀጋዬ ወንድሙ (አግሮን) በዛሬው ዕለት በፅህፈት ቤቱ በአንድ ዓመት ውል ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መቅጠሩን ክለቡ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልጿል፡፡


በተጫዋችነት ዘመኑ ለንግድ ባንክ እና ለኢትዮጵያ ወጣት ብሔራዊ ቡድን ተሰልፎ መጫወት የቻለው ፀጋዬ ወደ አሰልጣኝነቱ ጎራ ብቅ ካለ በኃላ የመከላከያ ሴቶች ቡድንን ዋና አሰልጣኝ፣ 2007 የመድን ረዳት አሰልጣኝ እንዲሁም ደግሞ ያለፉትን ዓመታት አቃቂ ቃሊቲን ከአንደኛ ሊግ በማሳደግ በከፍተኛ ሊግ ቆይታ አድርጓል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!