ሽመልስ በቀለ ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር ልምምድ ጀምሯል

ሽመልስ በቀለ በዛሬው ዕለት ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር የመጀመርያ ልምምዱን አድርጓል።

በዕለተ ሰንበት እረፍት አድርገው የዋሉት ዋልያዎቹ ዛሬ ባረፉበት የካፍ አካዳሚ ረፋድ ላይ ልምምዳቸውን ያከናወኑ ሲሆን በልምምዱ ወቅት ለግብፅ ሊግ ለምስር አልማቃሳ እየተጫወተ የሚገኘውና ቡድኑን ሳይቀላቀል የቆየው ሽመልስ በቀለ መካተቱን አረጋግጠናል።

በሌላ ዜና ሙጂብ ቃሲም እና አማኑኤል ዮሐንስ አሁንም ለብቻቸው ተነጥለው ልምምዳቸውን መስራታቸውን ሲቀጥሉ ሌሎቹ የቡድኑ አባላት በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ችለናል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!