ዋልያዎቹ በኒያሜ የመጀመርያ ልምምድ አከናውነዋል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በኒጀር የመጀመሪያ ልምምዳቸውን ሰርቷል።

ለካሜሩኑ የ2021 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ሦስተኛ የምድብ ጨዋታ ትናንት ወደ ሥፍራው ያቀናው ብሔራዊ ቡድኑ ከሰዓት በኋላ ኒያሜ መድረሱ የሚታወስ ሲሆን በኑም ሆቴል ማረፊያውን አድርጎ ዛሬ 10 ሰዓት ላይ በብሔራዊ ስታዲየም ግቢ ውስጥ በሚገኝ የመለማመጃ ሜዳ የመጀመርያ ልምምድ ማከናወኑን ፌዴሬሽኑ ገልጿል። ዋልያዎቹ ሜዳው ለልምምድ ምችት የማይሰጥ ቢሆንም የልምምድ ፕሮግራሙን በአግባቡና በከፍተኛ ፍላጎት ማከናወናቸውንም ጨምሮ ገልጿል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!