ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | አዲስ አበባ ከተማ የአሰልጣኞቹን ውል ሲያድስ በርካታ አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል

አዲስ አበባ ከተማ የዋና እና ረዳት አሰልጣኙን ውል ሲያድስ አስራ ዘጠኝ አዳዲስ እና አምስት ነባር ተጫዋቾችን አስፈርሟል፡፡

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን ተወዳዳሪ የሆነው አዲስ አበባ ከተማ ካለፈው አመት በተሻለ ተፎካካሪ ለመሆን በማሰብ ጠንካራ ሥራዎችን መሥራት ጀምሯል፡፡ የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ ነፃነት ታከለ በተለይ ለሶከር ኢትዮጵያ እንደገለፁት ከዓምናው የተሻለ እና ጠንካራ ቡድን ለመገንባት በማሰብ ከወዲሁ ትኩረት ሰጥተው መሥራት እንደጀመሩ ገልፀውልናል፡፡ ይህንንም በማሰብ የአሰልጣኞቹም ውል መራዘሙንም ሆነ በርካታ ተጫዋቾች መፈረማቸውንም ነግረውናል፡፡ ቡድኑን ዓምና በዋና አሰልጣኝነት ስትመራ የነበረችው የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ሙሉጎጃም እንዳለ እና ረዳቷ የሺሃረግ ለገሰ ለተጨማሪ አንድ ዓመት ውላቸውን አድሰዋል፡፡

ክለቡ የአሰልጣኞቹን ውል ከማራዘሙ ባሻገር 19 አዳዲስ ተጫዋቾችን ከተለያዩ ክለቦች አስፈርሟል፡፡

ግብ ጠባቂዎች:- ገነት አንተነህ (ከመከላከያ)፣ ቤተልሄም ዮሐንስ (ከጌዲኦ ዲላ)፣ ተስፋነሽ ተገኔ (ከአርባምንጭ ከተማ)

ተከላካዮች :- በሻዱ ረጋሳ (ከጌዲኦ ዲላ)፣ የውብዳር መስፍን (ከአቃቂ ቃሊቲ)፣ አበበች በተራ (ከአቃቂ ቃሊቲ)፣ አብነት ለገሰ (ከፋሲል ከነማ)፣ ዝናቧ ሽፈራው (ከአርባምንጭ ከተማ)፣ ሩታ ያደታ (ከጥረት)

አማካዮች:- መሠረት ገብረእግዚአብሔር (ከአቃቂ ቃሊቲ)፣ ትርሲት መገርሳ (ከጌዲኦ ዲላ)፣ ሀና ቱርጋ (ከኤሌክትሪክ)፣ እማዋይሽ ይመር (ከኤሌክትሪክ)፣ ፍሬወይኒ ገብረዮሐንስ (ከመቐለ)

አጥቂዎች:- መስታወት አመሉ (ከልደታ)፣ ሰላማዊት ኃይሌ (ከአቃቂ ቃሊቲ)፣ ድንቅነሽ በቀለ (ከጌዲኦ ዲላ)፣ ቤተልሄም ታምሩ (ከንግድ ባንክ)፣ ቤተልሄም አምሳሉ (ከፋሲል ከነማ)

ውል ያራዘሙ ነባር ተጫዋቾች :- እታገኝ ሰይፉ፣ እምወድሽ አሸብር፣ ዮርዳኖስ ፍሰሀ፣ ፍቅርተ አስማማው እና ቤተልሄም ሰማን

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!