ሰበታ ከተማ ወጣት ተጫዋች አስፈረመ

ተስፈኛው አጥቂ ዱሬሳ ሹቢሻ ለሰበታ ከተማ የሶስት አመት ኮንትራት ፈረመ፡፡

በአዳማ ከተማ ከ20 ዓመት በታች ቡድን ውስጥ ሲጫወት የነበረው እና ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴን በማድረግ ከብዙዎች አድናቆት የተቸረው ተጫዋች የተሰረዘውን የ2012 የውድድር ዓመት በውሰት ለከፍተኛ ሊጉ አርሲ ነገሌ ሲጫወት የነበረ ሲሆን ወደ አዳማ ውሰቱን ጨርሶ ቢመለስም አሳዳጊ ክለቡ ተጫዋቹን በመልቀቁ ሰበታዎች በሦስት ዓመታት ውል የግላቸው አድርገውታል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!