ከፍተኛ ሊግ | ስልጤ ወራቤ የአሰልጣኙን ውል ሲያራዝም አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈረመ

የከፍተኛ ሊጉ ክለብ ስልጤ ወራቤ የአሰልጣኙ እና ሦስት ነባር ተጫዋቾችን ውል ሲያራዝም ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል፡፡

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሐ ተደልድለው ከሚወዳደሩ ክለቦች መካከል አንዱ የሆነው ስልጤ ወራቤ የወጣቱ አሰልጣኝ አብዱልወኪል አብዱልፈታህን ኮንትራት ለተጨማሪ አንድ ዓመት ያራዘመ ሲሆን ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችንም አስፈርሟል፡፡ ግብ ጠባቂው መኳንንት አሸናፊን ከወላይታ ድቻ፣ የቀድሞው የአርባምንጭ እና የሀምበሪቾ ተከላካይ በረከት ቦጋለን እንዲሁም አጥቂው አላዛር ዝናቡን ከነገሌ አርሲ አዳዲስ ፈራሚ አድርጎ ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል፡፡

ተመስገን ዱባ (አጥቂ)፣ አማኑኤል ተፈራ (አጥቂ)፣ ጢሞቲዮስ ቢረጋ (ተከላካይ) ውላቸውን ያራዘሙ ነባር ተጫዋቾች ናቸው፡፡

©ሶከር ኢትዮጵያ