​ከፍተኛ ሊግ | ደሴ ከተማ አራት ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የአራቱን ውል ደግሞ አድሷል

በቅርቡ አሰልጣኝ ያሬድ ቶሌራን የቀጠረው ደሴ ከተማ አራት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የአራት ነባሮችን ውልም አራዝሟል፡፡

በምድብ ሀ በከፍተኛ ሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ ከሆኑ ክለቦች መካከል አንዱ የሆነው ደሴ ከተማ ለ2013 ራሱን ገንብቶ ለመቅረብ በቅርቡ አሰልጣኝ ያሬድ ቶሌራን ለአንድ ዓመት የቀጠረ ሲሆን የረዳት አሰልጣኙ ዮናታን በትረንም ውል ማራዘሙ ይታወሳል፡፡ ክለቡ አሰልጣኝ ያሬድ ቶሌራን ከቀጠረ በኃላ ክፍተት አለብኝ ባለው ቦታ አራት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የአራት ነባር ተጫዋቾችን ውል ደግሞ ለተጨማሪ ዓመት ለማቆየት ውል አድሷል፡፡

አዳዲስ ፈራሚዎች:- አንተነህ ሀብቴ (ግብ ጠባቂ ከለገጣፎ)፣ ሳሙኤል ወንድሙ (ተከላካይ ከአክሱም)፣ አንተነህ ተስፋዬ (አማካይ ከመድን)፣ ልዑል አስፋው (አጥቂ ከአክሱም ከተማ)

ውል ያደሱ:- በረከት አድማሱ (ተከላካይ፣ አክዌር ቻም (አጥቂ)፣ በድሉ መርዕድ (አማካይ)፣ ቶስላች ሳይመን (የተከላካይ አማካይ)

©ሶከር ኢትዮጵያ