​ከፍተኛ ሊግ | አዲስ አበባ ከተማ አዲስ ዋና አሰልጣኝ ሾሟል

ከከፍተኛ ሊጉ ምድብ ለ ክለቦች አንዱ የሆነው አዲስ አበባ ከተማ ረዳት አሰልጣኝ በመሆን ከ2010 ጀምሮ ሲሰራ የነበረው እስማኤል አቡበከርን ቀጥሯል፡፡ 

በተጫዋችነት ዘመኑ ኢትዮጵያ ቡና፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሀዋሳ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ ክለቦች በአጥቂ እና አማካይ ስፍራ ላይ ድንቅ ጊዜያት ካሳለፈ በኋላ በሚሌንየሙ መግቢያ ከተጫዋችነት ተገልሎ የሀረር ሲቲን ክለብ በረዳት አሰልጣኝነት በመያዝ የአሰልጣኝኘት ጅማሮ ያደረገው እስማኤል በ2009 በወቅቱ የአዲስ አበባ ከተማ አሰልጣኝ አሥራት አባተ ረዳት በመሆን ክለቡን ተቀላቅሎ ሲሰራ ከቆየ በኃላ ለዘንድሮ የውድድር ዓመት ክለቡን በአንድ ዓመት ውል በዋና አሰልጣኝነት ለማገልገል ፊርማውን አኑሯል፡፡ ክለቡ ከዋና አሰልጣኙ በተጨማሪ ከ20 ዓመት ቡድን አሰልጣኝ የነበረው ደምስን ረዳት አድርጎ ሽሟል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ