ከፍተኛ ሊግ | ቤንችማጂ ቡና የአሰልጣኙን ውል ሲያራዝም አዳዲስ ተጫዋቾችንም አስፈርሟል

የከፍተኛ ሊጉ ክለብ ቤንችማጂ ቡና የአሰልጣኝ ወንዳየው ኪዳኔን ኮንትራት ሲያራዝም አዳዲስ እና ነባር ተጫዋቾችን አስፈርሟል፡፡

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ ስር የሚገኘው ቤንችማጂ ቡና ለዘንድሮው የውድድር ዓመት የአሰልጣኝ ወንዳየው ኪዳኔን ውል ለተጨማሪ አመት ያራዘመ ሲሆን ዘጠኝ አዳዲስ ተጫዋቾችን በአዲስ መልክ አስፈርመዋል። የአስራ አምስት ነባሮችን ውል ደግሞ ለተጨማሪ ዓመት አድሷል፡፡

አዲስ ፈራሚዎች

ዘላለም ሊካሳ (ከደደቢት ግብጠባቂ)፣ ጆንቴ ገመቹ (ተከላካይ ከአርባምንጭ)፣ ካሳዬ በቀለ (ከካፋ ቡና ተከላካይ)፣ መቆያ አልታዬ (ከሀምበሪቾ ተከላካይ)፣ አሸናፊ ካሳ (ኮልፌ ቀራኒዮ አማካይ)፣ ጥላሁን በቀለ (ከኢኮሥኮ አማካይ)፣ ዳንኤል ተገኝ (ከጌዲኦ ዲላ አማካይ)፣ አበበ ታደሰ (ከየካ አጥቂ)፣ ወንድማገኝ ኪራ ከኢኮሥኮ አጥቂ)

ከአዳዲስ የክለቡ ተጫዋቾች በተጨማሪ የወሳኝ ተጫዋቾቹ ኦኒ ኡጁሉ፣ ሀቁምንይሁን ገዛኸኝ፣ ሌሊሳ ታዬ እና ተዘራ ጌታቸውን ጨምሮ የአስራአንድ ነባሮችን ውል አራዝሞ በዛሬው ዕለት ልምምዱን ጀምሯል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ