ሊዲያ ታፈሰ የቻን ዳኞች ዝርዝር ውስጥ ተካተተች

ኢትዮጵያዊቷ ጠንካራ ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ በ2021 ለሚደረገው የቻን ውድድር ላይ ከሚመሩ 19 ዳኖች ውስጥ ብቸኛዋ ሴት የመሐል ዳኛ ሆና ተካታለች። 

ካፍ ከወራት በፊት በካሜሩን አስተናጋጅነት ሊካሄድ በነበረው የአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) ውድድር ላይ ጨዋታዎችን እንዲመሩ ለቅድመ ስልጠና ከመረጣቸው ዳኞች መካከል ሊዲያ አንዷ የነበረች ሲሆን በመጨረሻው ዝርዝር ውስጥ ከተመረጡ 19 የመሐል ዳኞች ውስጥ ተካታለች። ባለ ልምዷ ዳኛ በካሜሩኑ ውድድር ላይ ከተመረጡ ዳኞት ብቸኛዋ ሴት የመሐል ዳኛ ስትሆን ከኢትዮጵያም ብቸኛዋ ናት። በቅርቡ ለዓለም ዋንጫ በዳኝነት እንዲያገለግሉ ከተመረጡ ዳኞች መሀል አንዷ የነበረችው እንስቷ አሁንም በሌላ ስኬት ዳግም ብቅ ብላለች፡፡

በረዳት ዳኞች በኩል 20 ዳኞች የተመረጡ ሲሆን ከኢትዮጵያ አንድም ዳኛ አልተካተተም። በተጨማሪም ከማላዊ፣ ናይጄርያ እና ካሜሩን የተመረጡት ሦስቱ ዳኞች ሴቶች ናቸው። 

ከዳኞቹ በተጨማሪ በVAR ዳኝነት ስምንት ዳኞች በካፍ ሲመረጡ ኢትዮጵያዊው ባምላክ ተሰማ ከዝርዝሩ ውስጥ ተካቷል።

ሊዲያ እና ሌሎች የተመረጡ ዳኞች ከአንድ ወር በኋላ ጃንዋሪ 11 ተሰባስበው የቅድመ ውድድር ኮርስ እንደሚወስዱ ታውቋል። 

© ሶከር ኢትዮጵያ