ወደ ጅማ ያቀናው የሊግ ኩባንያው ልዑክ ቡድን ግምገማውን አጠናቆ ተመለሰ

የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር ሁለተኛው የሚካሄድባት ከተማ ለግምገማ አቅንቶ የነበረው የሊግ ኩባንያው የልዑክ ቡድን ግምገማውን አጠናቆ ተመለሰ።

በአምስት በተመረጡ ከተሞች የሚካሄደው የዘንድሮው የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ለአንድ ወር የሚቆየውን ሁለተኛ ዙር ማለትም ከሰባተኛ እስከ አስራ አንደኛ ሳምንት ያሉ ጨዋታዎችን ለማስተናገድ የተመረጠችው ጅማ ከተማ መሆኗ ይታወሳል። ይህን ተከትሎ የሊግ አክሲዮን ማኅበሩ የጀማ ከተማ የሆቴል የሜዳዎች እና አጠቃላይ ቅድመ ዝግጅቱን አስመልክቶ ግምገማዎችን ለማድረግ በአቶ ክፍሌ የሚመራው የሊግ ኩባንያው የልዑክ ቡድን ማክሰኞ ወደ ስፍራው በማቅናት ያለውን አጠቃላይ ሁኔታ በመገምገም ተመልሷል። በጉብኝቱ ወቅት ያለውን የሆቴል የመጫወቻ ሜዳ እና የልምምድ ሜዳዎችን እንዲሁም የኮቪድ ህክምና ማዕከልን ቅኝት ያደረገ ሲሆን እግረ መንገዱንም ከከተማው ከንቲባ አቶ ቲጃኒ ጋር ውይይት አድርጓል።

ከጉብኝቱ በኃላ እንዳገኘነው መረጃ ከሆነ ውድድሩን ለማዘጋጀት ጅማ ከተማ አብዛኛዎቹን ነገሮች እንዳሟላች እና አንዳንድ ጥቃቅን የሚስተካከሉ ነገሮች በቀጣይ ቀናት እንዲስተካከሉ ምክረ ሀሳብ በመስጠት የልዑክ ቡድኑ ትናንት ማምሻውን አዲስ አበባ ገብቷል።


© ሶከር ኢትዮጵያ