ዜና እረፍት| እውቁና አንጋፋው የእግርኳስ ዳኛ ዐረፉ

ለበርካታ ዓመታት በኢትዮጵያ ዳኝነት ታሪክ ውስጥ ጨዋታ ከመምራት አንስቶ የጨዋታ ታዛቢ በመሆን እና በርካታ ዳኞችን አስተምሮ በማብቃት የሚታወቁት ብርቱዉ ሰው ዓለም ንፀብህ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

በኢንተርናሽናል ዳኝነት ዘመናቸው በተለያዩ ከፍተኛ ውድድሮች ላይ በብቃት ያዳኙት ጋሽ ዓለም ንፀብህ ያለፉትን ዓመታት ባጋጠማቸው ህመም ምክንያት በአልጋ ላይ በመሆን ህክምናቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ሲሆን ዛሬ ንጋት ላይ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተሰምቷል።

የእኝህ ታላቅ ዳኛ የቀብር ሥነ ስራዐት ዛሬ ታህሳስ 26 ቀን በ09:00 በቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት የሚፈፀም ይሆናል።

ሶከር ኢትዮጵያ በቀድሞ አንጋፋ ዳኛ ህልፈት የተሰማትን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀች ለቤተሰቦቻቸው፣ ለባልደረቦቻቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናትን ትመኛለች።


© ሶከር ኢትዮጵያ