ከፍተኛ ሊግ | የምድብ ለ ሁለት ጨዋታዎች ዛሬ አይደረጉም

በከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ ዛሬ ሦስት ጨዋታዎች እንደሚደረጉ በመርሃግብሩ ላይ አስቀድሞ የተገለፀ ቢሆንም ሁለቱ ጨዋታዎች ግን በኮቪድ 19 ምክንያት ወደ ሌላ ቀን ተሸጋግረዋል፡፡

በዛሬው ዕለት በስምንተኛ ሳምንት መርሀ ግብር መሠረት ሦስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ ተብሎ የነበረ ቢሆንም በኮቪድ 19 ዋነኛ ምክንያት ወዳልታወቀ ቀን ተሸጋግረዋል፡፡ ረፋድ 4፡00 በካፋ ቡና እና ጋሞ ጨንቻ መካከል ሊደረግ የነበረው ጨዋታ ሁለቱም ክለቦች ሜዳ ላይ አሟሙቀው እና ዳኞችም ፈትሸው ካጠናቀቁ በኋላ የኮቪድ 19 ውጤት አልደረሰም በሚል ጨዋታው ሳይደረግ ቀርቷል፡፡

ሌላኛው ከሰዓት 8፡00 በነቀምት ከተማ እና ጅማ አባቡና መካከል ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀው ጨዋታም የነቀምት ከተማ በርካታ ተጫዋቾች ቫይረሱ የተገኘባቸው በመሆኑ ሳይደረግ ወደ ሌላ ቀን ተሸጋግሯል፡፡ ቀን 10፡00 ሲል ግን በአዲስ አበባ ከተማ እና ኢኮሥኮ መካከል የሚደረገው ጨዋታ በተያዘለት መርሀ ግብር መሠረት እንደሚደረግ ሶከር ኢትዮጵያ ከአወዳዳሪው አካል ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ