አሰልጣኝ ውበቱ ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ሁለተኛ ዙር ዝግጅት 28 ተጫዋቾች ጠሩ

በመጋቢት ወር ከማዳጋስካር እና አይቮሪኮስት ጋር የሚጫወተው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለሚያደርገው ሁለተኛ ዙር ዝግጅት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ 28 ተጫዋቾች ጠርተዋል።

በወሩ መጀመርያ በጅማ በነበረው የአጭር ጊዜ ዝግጅት 28 ተጫዋቾች ተጠርተው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን በአማካይ እና አጥቂ ስፍራ ላይ ሁለት ለውጦች ብቻ ተደርገዋል። በዚህም ኤልያስ ማሞ እና ዳዋ ሆቴሳ ባለፈው ምርጫ የነበሩና አሁን የተዘለሉ ሲሆን አማኑኤል ዮሐንስ እና መስፍን ታፈሰ በምትካቸው ተካተዋል።

የብሔራዊ ቡድኑ ዝግጅት የጅማው የፕሪምየር ሊግ ውድድር ከተጠናቀቀ በኋላ ከየካቲት 1 እስከ 6 በካፍ የልህቀት ማዕከል እንደሚከናወን ፌዴሬሽኑ አሳውቋል።

ዝርዝር

ግብ ጠባቂዎች

ተክለማርያም ሻንቆ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ጀማል ጣሰው (ወልቂጤ)፣ ፍሬው ጌታሁን (ድሬዳዋ)፣ ፋሲል ገብረሚካኤል (ሰበታ ከተማ)

ተከላካዮች

ሱሌይማን ሀሚድ (ሀዲያ ሆሳዕና)፣ አሥራት ቱንጆ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ አስቻለው ታመነ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ያሬድ ባየህ (ፋሲህ ከነማ)፣ ቶማስ ስምረቱ (ወልቂጤ ከተማ)፣ ወንድሜነህ ደረጄ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ኤልያስ አታሮ (ጅማ አባ ጅፋር)፣ ረመዳን የሱፍ (ወልቂጤ ከተማ)፣ አምሳሉ ጥላሁን (ፋሲል ከነማ)

አማካዮች

ታፈሰ ሰለሞን (ኢትዮጵያ ቡና)፣ መስዑድ መሐመድ (ሰበታ ከተማ)፣ አብዱልከሪም ወርቁ (ወልቂጤ ከተማ)፣ ሀብታሙ ተከስተ (ፋሲል ከነማ)፣ ሀይደር ሸረፋ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ፍፁም ዓለሙ (ባህር ዳር ከተማ)፣ ጋዲሳ መብራቴ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ሽመክት ጉግሳ (ፋሲል ከነማ)፣ አማኑኤል ዮሐንስ (ኢትዮጵያ ቡና)

አጥቂዎች

ጌታነህ ከበደ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ አቤል ያለው (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ አቡበከር ናስር (ኢትዮጵያ ቡና)፣ አማኑኤል ገብረሚካኤል (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ መስፍን ታፈሰ (ሀዋሳ ከተማ)፣ ሙጂብ ቃሲም (ፋሲል ከነማ)

© ሶከር ኢትዮጵያ